About Asdenaki

Asdenaki is a 17-year-old boy from Bansa, a small village in the southern part of Ethiopia. His mom passed away when he was 4 years old, and his dad is blind. He comes from a very poor family. Since his blind father could not support him financially, Asdenaki is dependent on his uncle for educational and financial support. 

His condition

Asdenaki suffered from an acute obstruction of blood from his left ventricle due to a congenital anomaly of the right coronary sinus (which are critical to providing oxygenation to the heart itself).

As you can see from the video taken prior to his surgery, he was severely ill that he could barely walk or take enough breath to speak. He needed an emergency open-heart surgery in order to survive

What was needed to save his life?

Asdenaki had an aneurysm (enlargement of an artery caused by a weakening of the artery wall) blockage in his artery and needed an urgent heart surgery called unroofing of the right coronary artery. This kind of surgery is very rare throughout the world.  

Except for the wealthy who can pay for surgery out of their pocket, such urgent cases go untreated in Ethiopia. Open heart surgeries are not usually available on an emergency basis in Ethiopia. Healing Valves Ethiopia organized a team of cardiac care professionals for an urgent operation to save Asdenaki’s life.  

It would have been impossible to save Asdenaki’s life without the volunteer professionals of Healing Valves Ethiopia and the financial help of donors to Healing Valves North America. 

Surgery/procedure plan and execution

His surgery took more than four hours with an effective performance by the local team of volunteers led by cardiac surgeon Dr. Fekede Agwar. The initial plan was to fix the aneurysm with the likely replacement of the aortic valve. However, the surgeon successfully repaired the aneurysm without replacing Asdenaki’s native valve. 

This was great news for Asdenaki because he will not need to continually take blood-thinning medicine which he would have had to do if his valve was replaced with a mechanical one. 

Asdenaki – The first day after the operation

Post-surgery progress

Asdenaki had a quick recovery. He was discharged from the hospital three days after the surgery with a big smile on his face. Asdenaki is doing great now and is back in Hawassa to live with his uncle. For his routine post-surgery follow-ups, Asdenaki sees cardiologists in Hawassa who collaborate with Dr. Fekede. 

Thank you!

Healing Valves North America made a call for donors to help pay for Asdenaki’s surgery. With donors from USA and Ethiopia, the needed funds were raised to provide Asdenaki with lifesaving care. If it were not for the frantic efforts of both Healing Valves Ethiopia and Healing Valves North America, Asdenaki would not be alive today. 

We are forever grateful for all the financial support you make to Healing Valves North America. You are saving a life and giving a gift of life to those who need it most.

ስለ አስደናቂ

አስደናቂ በኢትዮጵያ ደቡባዊ ክፍል በምትገኝ ቦባንሳ በተባለች አነስተኛ መንደር የተወለደ ወጣት ልጅ ነው፡፡ እናቱ ልጁ የ4 ዓመት እያለ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች ሲሆን አባቱ ዓይነ ስውር ናቸው፡፡ የተገኘው በጣም ደሀ ከሆኑ ቤተሰቦች ነው፡፡ ዓይነ ስውር አባቱ የገንዘብ ድጋፍ ሊያደረጉለት ስለማይችሉ አስደናቂ ለትምህርት እና ለገንዘብ ድጋፍ በአጎቱ ላይ ጥገኛ ነው፡፡

ሁኔታው

አስደናቂ በግራ ደም መልስ መስመሩ ላይ ባለበት የቀኝ ኮርናል ሳይነስ ችግር (በጣም ስር የሰደደ እና ለልቡ ለራሱ ኦክስጅን ድጋፍ ያስፈልገዋል)፡፡

ከቀዶ ህክምናው በፊት በተቀረጸው ቪዲዮ ላይ እንደምትመለከቱት በጣም ከባድ ህመም ያለበት ሲሆን በተጨማሪም ለመራመድ የሚቸገር እንዲሁም ለመናገር የሚያስፈልገውን ትንፋሽ ለመሳብ ችግር እንዳለበት ያሳያል፡፡ ለመትረፍ ድንገተኛ የልብ ክፍት ቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡

ህይወቱን ለማዳን ምን ያስፈልጋል?

አስደናቂ በደም ቅዳ ግድግዳ መሳሳት ምክንያት የደም ቅዳ መስመር መተለቅ ያጋጠመው ሲሆን ይህም የደም ቅዳ ቧንቧው ደም እንዳያመላልስ ያደረገው በመሆኑ አስቸኳይ አንሩፊንግ ኦፍ ራይት ኮሮናሪ አልትሪ የተሰኘ የቀዶ ህክምና ያስፈልገዋል፡፡ የዚህ አይነት ቀዶ ህክምና በዓለም ላይ እጅግ አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ነው፡፡

ለዚህ ህክምና ከኪሳቸው አውጥተው ለመክፈል ከሚችሉ ሀብታሞች በስተቀር የዚህ አይነት አስቸኳይ ህክምና በኢትዮጵያ ውስጥ አይሰጥም፡፡ የልብ ክፍት ቀዶ ህክምናዎች በድንገተኛ ሁኔታ በኢትዮጵያ ውስጥ አዘውትረው አይገኙም፡፡ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት የተባለ ድርጅት የልብ እንክብካቤ ፕሮፌሽናሎች አስደናቂን ህይወት ለማትረፍ የተዋቀረ ቡድን ነው፡፡

የአስደናቂ ህይወት ያለ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ በጎ ፈቃደኛ ፕሮፌሽናል ሀኪሞች እና ከሰሜን አሜሪካ ሂሊንግ ቫልቭስ የገንዘብ ድጋፍ በስተቀር ማትረፍ አይቻልም፡፡

ቀደሞ ህክምና/የአሰራር እቅድ እና አፈጻጸም

የቀዶ ህክምናው ከ4 ሰዓት በላይ የፈጀ ሲሆን በልብ ቀዶ ሀኪሙ ዶ.ር ፈቀደ አጓር የሚመራ የሀገር ውስጥ በጎ ፈቃደኞች ውጤታ አፈጻጸም ተከናውኗል፡፡ የመጀመሪያው እቅድ ያለበትን የደም ቅዳ ቧንቧ መሳሳት አወርቲክ ቫልብን መተካት ነበር፡፡ ሆኖም ቀዶ ሀኪሙ የአስደናቂን የተፈጥሮ ቫልቭ ሳይቀይሩ ራሱን በተሳካ ሁኔታ መጠገን ችለዋል፡፡

ይህ የአስደናቂ እጅግ ትልቅ ዜና ምክንያቱም የተፈጥሮ የደም ቅዳ ቧንቧው በመካኒካል ቫልቭ ቢቀየር ኖሮ በየጊዜው የደም ማቅጠኛ መድሀኒት እድሜ ልኩን መውሰድ ይኖርበት ስለነበር ነው፡፡

ከቀዶ ህክምና በኋላ ያለ እድገት

አስደናቂ በፈጣን ሁኔታ አገግሟል፡፡ ከሆስፒታል ቀዶ ህክምና ከተደረገለት በኋላ በፊቱ ላይ ጉልህ ፈገግታ እየታየ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ አስደናዊ በአሁን ጊዜ በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን አሁን ከአጎቱ ጋር ለመኖር ወደ ሀዋሳ ተመልሷል፡፡ ከቀዶ ህክምና በኋላ ላለው የህክምና ክትትል አስደናቂ ከዶ/ር ፈቀደ ጋር በመተባባር በሀዋሳ የሚገኙ የልብ ሀኪሞችን ይጎበኛል፡፡

እናመሰግናለን!

የሰሜን አሜሪካ ሂሊንግ ቫልቭስ ማህበር አስደናቂን ቀዶ ህክምና ለመሸፈን ለጋሾችን ጠርቷል፡፡ ከዩኤስ አሜሪካ እና ከኢትዮጵያ የተገኙ ለጋሾች አስፈላጊውን ገንዘብ ያበረከቱ ሲሆን የአስደናቂን የህይወት አድን የህክምና ወጪ ሸፍነዋል፡፡ ያለ ሂሊንግ ቫልቭስ ኢትዮጵያ እና ሂሊንግ ቫልቭስ ሰሜን አሜሪካ ከፍተኛ ጥረት ባይሆን ኖሮ በአሁኑ ጊዜ አስደናቂ በህይወት አይርም ነበር፡፡

የሰሜን አሜሪካ ሂሊንግ ቫልቭስ ማህበር ላበረከታችሁት የገንዘብ ድጋፍ ሁልጊዜም እናመሰግናችኋለን፡፡ ህይወትን አድናችሁ እጅግ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ህይወትን በስጦታ አበርክታችኋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *